(ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድ ዝግጅት ክትትል ግምገማ ዳይሬክቶሬትና የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት በጋራ በመሆን በእቅድ አዘገጃጀትና ሪፖርት ፤ በአገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር እንዲሁም በክትትልና ድጋፍ አሰጣጥ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
በስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ኃላፊ አማካሪና የዘርፉ ኃላፊ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ ለትምህርት ጥራትና ስኬት በጋራ የጠራ እቅድ ማቀድ እንዲሁም እቅድን በተግባር ላይ ማዋል ዋናው መሆኑን ጠቁመው ስልጠናው ቀድሞ ያላችሁን እውቀት በማዳበር ለትምህርት ሥራ ኃላፊነታችሁን በአግባቡ እንድትወጡ አቅም ይፈጥራል ብለዋል :: አያይዘውም የትምህርት ማህበረሰቡን በአግባቡ ለማገልገል እንዲቻል የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን በማከናወን ሂደት ከሌሎች ጋር በትስስር በመስራት መሪ እቅዳችንን ማሳካት እንዲቻል በስልጠናው የሚቀርቡ ሰነዶችን በአግባቡ በመከታተል በእውቀት ለመምራት ራሳን ማብቃት ይገባል ብለዋል::
የእቅድ ዝግጅት ክትትል ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ ስልጠናው በዋናነት ተጠሪ ተቋማት የሚያዘጋጁት እቅድና ሪፖርት ወጥነት እንዲይዝ ብሎም የትምህርት ሴክተሩ ተቀራራቢ አፈፃፀም እንዲኖረው ያስችላል ብለው የትምህርት አመራሩና ባለሙያው ተቀራራቢ ውጤቱን ለማምጣት የተሻለ እቅድና ሪፖርት እንዲያዘጋጅ ማስቻል የስልጠናው ዋና ግብ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ አያይዘውም ሰልጣኞች ከስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ተግባራዊ እንዲያደርጉና በቀጣይም ወቅቱን የጠበቀና ጥራት ያለው ተዋረዳዊ ሂደቱን የጠበቀ እቅድ ዝግጅትና ሪፖርት ልውውጥ እንዲኖር አሳስበዋል፡፡
የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋአገኘሁ ለገሰ በበኩላቸው የመልካም አስተዳደር ፤ ሌብነትና ብልሹ አሰራር እቅድ ዝግጅትና ወደ ተግባር የተገባበትን ሂደት ለማየት በተዘጋጀ ቼክሊስት ድጋፍና ክትትል መካሄዱን አስታውሰው በስልጠናው በሚቀርብ የድጋፍና ክትትል ግብረመልስ መሰረት የጋራ ውይይት እንደሚደረግ አብራርተዋል ፤ በግብረመልሱ መነሻነትም የማሻሻያ ስራዎች እንደሚሰሩ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
ስልጠናው የእቅድ ዝግጅት ክትትል ግምገማ ዳይሬክቶሬት ባለሙያ በወ/ሮ ገበያነሽ ተስፋዬ እና የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ በሆኑት በአቶ ሃፍቱ ብርሃኔ ለሁሉም ክፍለ ከተሞች ስራ አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች ፤ ለወረዳ ቡድን መሪዎችና ለሁለቱም ዳይሬክቶች ባለሙያዎች እየተሰጠ እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
0 Comments