በአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍትሀዊነት(GEQIP-E)ከ2010 እስከ 2015ዓ.ም ለአምስት አመታት የተከናወኑ ተግባራት ግምገማ ተካሄደ።

by | ዜና

(ቀን ህዳር 16/2016 ዓ.ም) ግምገማው በዋናነት አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍትሀዊነት (GEQIP-E) ፕሮግራም ትግበራ ከተጀመረበት ከታህሳስ 2010 ዓ.ም እስከ 2015 በጀት አመት ድረስ የተከናወኑ ተግባራትን በተለይም የውስጥ ቅልጥፍና ከማሻሻል  ፣የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ፣ የትምህርት ፍትሀዊነትና ተደራሽነትን እንዲሁም የተሻሻለ የአስተዳደር አቅም ከማጎልበት አንጻር  የተከናወኑ ዋና ዋና የፊዚካልና ፋይናንሺያል ተግባራት ፣የተመዘገቡ ውጤትቶች እና ያገጠሙ ችግሮችን በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ታስቦ መካሄዱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍትሀዊነት(GEQIP-E)ሪጅናል ኮርድኔተር  አቶ አሸናፊ ከበደ አስታውቀዋል።

አቶ አሸናፊ አክለውም በመርሀግብሩ በ2016 ዓ.ም የፕሮግራሙ እቅድ መሰረት በዝግጀትና ትግበራ ምዕራፎች የተከናወኑና እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት አፈጻጸምን በመገምገም በቀጣይ የሚጠበቁ ውጤቶችን አስመልክቶ በየደረጃው ከሚገኙ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ እንደሚካሄድ ገልጸው በአፈጻጸም ግምገማው በፕሮግራሙ አጠቃላይ ይዘት፣ በስነምግባርና ጸረሙስና ጽንሰ ሀሳብ እንዲሁም በፕሮግራሙ ትኩረት ተሰጥቶ ስለሚደገፉ የአጠቃላይ ትምህርት ICT የትግበራ ሂደትና የወደፊት የትኩረት እቅድ ዙሪያ ለተሳታፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱን አስገንዝበዋል።

በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ አቶ ታዬ ወልደኪዳን ከአይ ሲቲ ትምህርት አተገባበር ጋር በተገናኘ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሲሰጡ የስነምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክተር አቶ አስራት ሽፈራው የስነምግባርና ፀረሙስና ጽንሰ ሀሳብን በተመለከተ ስልጠና ሰተው የግምገማ መድረኩ ተሳታፊዎች በሁለቱ ቀናት በቀረቡ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።

በግምገማ መድረኩ ከኢፌድሪ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ፣ ከአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጥና ቁጥጥር ባለስልጣን  እንዲሁም የትምህርት ቢሮ  GEQIP-E ፕሮግራም ተግባሪ የስራ ክፍሎች ዳይሬክተሮችና የተግባሪ የስራ ክፍሎች የፕሮግራሙ ተጠሪዎች  ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 30
  • 222
  • 1,584
  • 6,364
  • 214,625
  • 214,625