የትምህርት ሚኒስቴር የ2016 የትምህርት ዘመን ትምህርት በሀገር አቀፍ ደረጃ መስከረም 14/1/2016 ዓ.ም እንደሚጀመርና ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች በራሳቸው መርሀ-ግብር ማስጀመር እንደሚችሉ መግለፁ ይታወቃል። ይሁን እንጂ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 የትምህርት ዘመን ትምህርት መስከረም 14 /1/2016 ዓ.ም እንደሚጀመር በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን እናሳውቃለን።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 የትምህርት ዘመን ትምህርት መስከረም 7 /1/2016 ዓ.ም በሁሉም ትምህርት ተቋማት ይጀመራል።

0 Comments