በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በሚሰጥባቸው የፈተና ጣቢያዎች የመስክ ምልከታ ተካሄደ።

by | ዜና

ቀን 27/1/2015 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በሚሰጥባቸው የፈተና ጣቢያዎች የመስክ ምልከታ ተካሄደ።

የመስክ ምልከታው በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ላም በረት አከባቢ በሚገኘው የኢፌድሪ ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲቲዩትና በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተካሄደ ሲሆን የትምህርት ሚኒስተር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱን ጨምሮ የቢሮው አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ እና የተቋማቱ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

የመስክ ምልከታው በዋናነት በተቋማቱ የተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ማወቅን መሰረት አድርጎ የተካሄደ ሲሆን የመፈተኛ ክፍሎች፣የመመገቢያ አዳራሾች እንዲሁም የመኝታ ክፍሎች ዝግጅት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ምልከታ ተካሂዶባቸዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በነገው እለት በተዘጋጀላቸው ተሽከርካሪ ወደፈተና ጣቢያዎች ገብተው በዩኒቨርሲቲዎቹ ኦረንቴሽን ተሰቷቸው የፊታችን ሰኞ ፈተናውን መፈተን እንደሚጀምሩ ቀደም ብሎ መገለጹ ይታወቃል።

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 0
  • 175
  • 2,114
  • 9,135
  • 234,185
  • 234,185