ሀምሌ 17/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን እቅድ አፈጻጸም እና በ2017 ዓ.ም ዕቅድ ዙሪያ በየደረጃው ከሚገኙ የትምህርት አመራሮች ጋር ለሶስት ቀናት የቆየው ግምገማና ውይይት ማጠቃለያ መድረክ ከተከናወነ በሃላ በከተማ አስተዳደሩ የተከናወኑ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡
የጉብኝቱ ተሳታፊዎች የተከናወኑ ፕሮጀክቶችን መመልከታቸው ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረባቸው ጠቁመው ፕሮጀክቶቹን እንዲመለከቱ እድል ላመቻቸላቸው ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምስጋና አቅርበዋል።
0 Comments