በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አዘጋጅነት ከሰኔ 9 እስከ 11/2014 ዓ.ም “የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ የብልጽግና ጉዟችንን በሳይንስ የፈጠራ ስራ እውን እናደርጋለን! ” በሚል መሪ ቃል በድምቀት ሲካሄድ የቆየው ከተማ አቀፍ የሳይንስ ፈጠራ አውደ ርዕይ በዛሬው እለት ተጠናቀቀ።

by | ዜና

ቀን 11/10/2014 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አዘጋጅነት ከሰኔ 9 እስከ 11/2014 ዓ.ም “የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ የብልጽግና ጉዟችንን በሳይንስ የፈጠራ ስራ እውን እናደርጋለን! ” በሚል መሪ ቃል በድምቀት ሲካሄድ የቆየው ከተማ አቀፍ የሳይንስ ፈጠራ አውደ ርዕይ በዛሬው እለት ተጠናቀቀ።

በመርሀ ግብሩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ባስተላለፉት መልዕክት ከተማ አቀፉ የሳይንስና ፈጠራ አውደ ርዕይ ከመክፈቻው ጀምሮ እስከ መዝጊያ ድረስ በደማቅና ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበው የዘንድሮው አውደ ርዕይ ሌሎች መሰል መርሀ ግብሮችንም በድምቀት ማክበር እንደምንችል ያሳየ መሆኑን አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸው ላለፉት ሶስት ቀናት በድምቀት ሲካሄድ የቆየው ከተማ አቀፍ የሳይንስ ፈጠራ አውደ ርዕይ በሀገራችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ባለምጡቅ አእምሮ ትውልድ እየተፈጠረ እንደሚገኝ ያሳየ መርሀ ግብር ከመሆኑ ባሻገር የሀገራችንን አንድነት የሚያጎለብቱ ትዕይንቶች የታዩበት መሆኑንም አስረድተዋል።

የመዝጊያ መርሀግብሩ የክብር እንግዳና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሀንስ ጫላ ባስተላለፉት መልዕክት በአውደ ርዕዩ በተማሪዎችና መምህራን ተዘጋጅተው ለዕይታ የቀረቡት የሳይንስ ፈጠራ ስራዎች ሀገራችንን ወዳሰበችው የብልጽግና ጉዞ የማሸጋገር አቅም እንዳላቸው ገልጸው ቢሯቸው ከትምህርት ሴክተሩ ጋር በጋራ መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

በመርሀ ግብሩ ማጠቃለያ በአውደ ርዕዩ በየትምህርት ደረጃው ውድድር በተደረገባቸው የፈጠራ ስራዎችና በሽብርቅ አሸናፊ ለሆኑ ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም ክፍለከተሞች ሽልማት የተሰጠ ሲሆን ለመርሀ ግብሩ ስኬታማነት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቶ ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 309
  • 374
  • 4,290
  • 15,620
  • 98,486
  • 98,486