(አዲስ አበባ 2/2/2016 ዓ.ም) ጉብኝቱ የካ ክፍለከተማ በሚገኘው ደጃዝማች ወንድይራድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተካሄደ ሲሆን በመርሀ ግብሩ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሚስተር ሬሚ መርችዋክስ ፣ የፊላንድ ሚሽን ምክትል ዳይሬክተር ሚስ ላራ ኔልቶናን ፣በአለም አቀፉ የምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ክሪስ ሪኮይ እንዲሁም በድርጅቱ የኢትዮጵያ የትምህርት ቤት ምገባ ዳይሬክተር ሀና ፒተርሰንን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።
በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሚስተር ሬሚ መርችዋክስ በጉብኝቱ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት የፈረንሳይ እና የፊላንድ መንግስታት በጋራ በመሆን በአለም አቀፍ ደረጃ 400 ሚሊየን የሚደርሱ ህጻናትን በትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ ማድረጋቸውን ገልጸው በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመተግበር ላይ የሚገኘው የትምህርት ቤት ምገባ ለሌሎች ተሞክሮ መሆን የሚችል ተግባር መሆኑን በጉብኝታቸው ማረጋገጣቸውን አስታውቀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ የቅድመ 1ኛ ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች በምገባ ፕሮግራሙ ተጠቃሚ መሆናቸውን እና ፕሮግራሙም በተማሪዎች ውጤት መሻሻል ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸው በአዲስ አበባ ተግባራዊ የሆነው የምገባ ፕሮግራም በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ማግኘቱንም አስገንዝበዋል።
የደጃችወንድይራድ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ሰለሞን ክቤ የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ከተጀመረ አንስቶ በትምህርት ቤቱ የተማሪዎች ውጤትም ሆነ ስነምግባር በከፍተኛ ደረጃ መሻሻሉን ጠቁመው ትምህርት ቤቱ የከተማ ግብርናን ተግባራዊ በማድረግ ለምገባ ፕሮግራሙ ድጋፍ የሚሆኑ ግብአቶችን በማቅርብ ላይ እንደሚገኝም አስረድተዋል።
0 Comments