በአዲስ አበባ ከተማ በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ፣ ትምህርት ቤቶችና ክፍለ ከተሞች ዕውቅና ተሰጠ።

by | ዜና

(ህዳር 11 ቀን 2016 ዓ.ም) በዕውቅና መርሀ – ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱን ጨምሮ የከተማው ካቢኔ አባላት ፣ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት  አመራሮች ፣ የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር  እና  የተማሪ ወላጅ ማህበር አመራሮች ፣ መምህራን ፣ ተሸላሚ ተማሪዎች እና ወላጆቻቸው ተገኝተዋል።

       

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በመርሀ-ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የዕውቅና መርሀ – ግብሩ ተሸላሚ ተማሪዎች በቀጣይ የትምህርት ህይወታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ከማስቻሉ ባሻገር በ2016 ዓ.ም የሚፈተኑ ተማሪዎችን ተነሳሽነት ከፍ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸው የዘንድሮ ተሸላሚ ተማሪዎች በቀጣይ በሚገቡባቸው ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን በላቀ ውጤት ለማጠናቀቅ ከወዲሁ ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፉ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት በተማሪዎች ውጤት  በተለይም በ6ኛ እና 8ኛ ክፍል አበረታች ውጤት መመዝገቡን ጠቁመው በ12ኛ ክፍል የሚፈለገውን ያህል ውጤት ባይመዘገብም በቂ ዝግጅት ከተደረገ ውጤታማ መሆን እንደሚቻል የዛሬ ተሸላሚ ተማሪዎች ማረጋገጫ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

በመርሀ- ግብሩ በተፈጥሮ ሳይንስ 600 እና በላይ ያስመዘገቡ 97 ተማሪዎች፣በማህበራዊ ሳይንስ 450 እና በላይ ያስመዘገቡ 66 ተማሪዎችን፣ 6 አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች፣9ትምህርት ቤቶችና 3ክፍለ ከተሞችን ጨምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተፈጥሮ ሳይንስ ከፍተኛውን 649 ውጤት ያስመዘገበችው ተማሪ ሀናን ነጃ አህመድ ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።

ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡት ተማሪዎች ላፕቶፕ ኮምፒውተርን ጨምሮ ታብሌት ስልኮች ሲሸለሙ በርካታ ተማሪ ያሳላፉ ትምህርት ቤቶችና የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች ዋንጫና የምስክር ወረቀት ከክብርት ከንቲባዋና ከትምህርት ቢሮ ኃላፊው ተበርክቶላቸዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 1
  • 44
  • 222
  • 1,598
  • 6,378
  • 214,639
  • 214,639