በትምህርት ተቋማት ክትትልና ቁጥጥር ለሚያካሂዱ ሱፐርቫይዘሮችና የኢንስፔክሽን ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ተሰጠ።

by | ዜና

(ግንቦት 6 ቀን 2016 ዓ.ም) የክትትልና ቁጥጥር መርሀ ግብሩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በጋራ የተዘጋጀ ቼክ ሊስትን መሰረት አድርጎ የሚካሄድ ሲሆን ክትትሉ ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀን በሁሉም የመንግስትና የዕቅና ፍቃድ ባላቸው የግል ትምህርት ቤቶች እንደሚካሄድ  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ አድማሱ ደቻሳ ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ በትምህርት ቤቶች ተደጋጋሚ የድጋፍና ክትትል ሲካሄድ መቆየቱን ገልጸው በአሁኑ ቁጥጥርና ክትትል እስካሁን የተካሄዱ የድጋፍ ሂደትን መሰረት በማድረግ የተሰጡ ግብረ መልሶች ተቋማቱን ምን ያህል ውጤታማ እንዳደረጉ በማየት የትውልድ ግንባታ ሂደቱ የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ ማድረግ እንደሚገባ አስረድተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳኘው ገብሩ በበኩላቸው የቁጥጥር መርሀ ግብሩ ትምህርት ተቋማቱ ስርአተ ትምህርቱን ምን ያህል በአግባቡ ተግባራዊ እያደረጉ እንደሚገኙ በማየት ለ2017ዓ.ም ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ እንዲቻል ታስቦ መዘጋጀቱን ጠቁመው ቁጥጥሩን ለማካሄድ የተመደቡ ባለሙያዎች ተልኳቸውን በቼክሊስቱ መሰረት በመወጣት ሪፖርት ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በአዲስ አበባ ከተማ በበይነ መረብ ኦን ላይን እንደመሰጠቱ ትምህርት ቤቶች በተለይም የግል ትምህርት ተቋማት ፈተናውን በአግባቡ ለመስጠት ግብአቶችን ከማሙዋላት ጀምሮ እያደረጉ የሚገኙትን የቅድመ ዝግጅት ስራ ማየት የቼክሊስቱ አካል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል አስታውቀዋል።

0 Comments

SITE VISITORS

  • 0
  • 183
  • 249
  • 2,419
  • 8,971
  • 243,953
  • 243,953