በትምህርት ተቋማት ላይ የተበላሹ የውሃ ቧንቧዎችን የሚጠግኑ ባለሙያዎችን ማሟላት የሚያስችል ፕሮፖዛል በስፕላሽ ኢንተርናሽናል ቀርቦ ውይይት ተካሄደ፡፡

by | ዜና

(ህዳር 7 ቀን 2016 ዓ.ም) በስኩል ወሽ ንቅናቄ “ውሃና ንጽህና በትምህርት ቤቶች ለሁሉም “ በሚል ፕሮጀክት መሰረት በሁሉም ትምህርት ቤቶች  ለተማሪዎች ንጹህና በቂ የውሃ አቅርቦት ለማድረስ እየተደረገ ያለውን ጥረት ይደግፋል የተባለ የውሃ ቧንቧዎችን የሚጠግኑ ባለሙያዎች  ማሟላት የሚያስችል ፕሮፖዛል ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊና ማኔጅመንት አባላት በስፕላሽ ኢንተርናሽናል  ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡

ሰፕላሽ ኢንተርናሽናል በውይይቱ ላይ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የሚገኙ የውሃ ቧንቧዎች በወቅቱና ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታ እንዲቀርብ ያስችላል ያለውን ፕሮፖዛል አቅርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን  በውይይቱ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ውስን ትምህርት ቤቶች የውሃ ቧንቧ ጥገና ባለሙያዎች ቢኖሩም በሁሉም ትምህርት ቤቶች በቂ ጥገና ለማድረግ የሚያስችል ባለመሆኑ የውይይት ሰነዱን ለቢሮው ማቅረብ ማስፈለጉ ተገልጻል፡፡ በቀረበው ፕሮፖዛል መሰረትም በሁሉም ትምህርት ቤቶች የሚገኙ የውሃ ማስተላለፊያ ቧንቧዎችና መስመሮችን በተመጣጣኝ ዋጋና የቁሳቁስ ወጪን በመቆጠብ የሚሰሩ የጥገና ባለሙያዎችን ለመቅጠር ያስችላል ተብላል፡፡

በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በትምህር ቤቶች የንጹህ ውሃ አቅርቦት የትምህርት ስራውን ስኬታማ ለማድረግ በሚደረጉ ጥረቶች ውስጥ አንዱና የከተማ አስተዳደሩም ዋና ትኩረት እንደሆነ ጠቁመው የቀረበው ፕሮፖዛል የሰራተኛ  ቅጥርን የሚመለከት በመሆኑ ከቢሮው ባለፈ የከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ቢሮ እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትንም ውይይት እንደሚፈልግ ተናግረዋል፡፡

 

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 0
  • 175
  • 2,114
  • 9,135
  • 234,185
  • 234,185