በትምህርት ቤቶችን ላይ የሚገኙ ግብዓቶችን ለመለየትና ለመመዝገብ  በሚያስችል  ሶፍትዌር ላይ  ያተኮረ ስልጠና መስጠት ተጀምራል፡፡

በእለቱ በትምህርት ቤቶች ያሉ መሰረተ ልማቶችን ለማሟላት ትልቅ ሃላፊነት ያለባችሁ የመስኩ ምሁራን ክፍተቶችን ለመሙላት አቅማችሁን ተጠቀሙ ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት  ቢሮ ሃላፊ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ የትምህርት  ሴክተሩ ራሱን በማዘመን ለትውልድ መማሪያ መሆን እንዲችል የአይሲቲ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የትምህርት ቤቶችን እድገት መገንባት  እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በትምህርት ቤቶች ላይ የሚገኙ መሰረተ ልማቶች በሚፈለገው ደረጃ አለመደራጀት በትምህርት ጥራት ላይ  ያለውን ችግር ለመቅረፍ እንቅፋት መሆኑን የገለፁት የትምህት ሚኒስቴር የSIP ባለሙያ አቶ ከተማ ቀውይ በበኩላቸው ትምህርት ቤቶችን በግብዓትና በመሰረተ ልማት የተሻለ ለማድረግና ስርነቀል ለውጥ ለማምጣት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማቀዱን ገልጸዋል፡፡ የሚዲያ ባለሞያዎችም ለዚህ ስራ ጋርነታቸውን ማሳየት አለባቸው በማለት ተናግረዋል፡፡ አክለውም በቀጣይ መረጃዎች ተሞልተው እንደተጠናቀቁ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሰፊ ንቅናቄ ይኖራል ብለዋል፡፡

ሁሉም ሰው የተማረበትን ትምህርት ቤት መረጃ በቀላሉ ማግኘት እንዲችል የተዘጋጀ ሶፍትዌር መሆኑን ያብራሩት የአዲስ  አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ከሚዩኒኬሽን ሶፍትዌርና ዳታ ማእከል ቡድን መሪ አቶ ታዬ ወ/ኪዳን  ስልጠናው ለአስር ቀናት የሚሰጥ መሆኑን ገልጸው ሰልጣኞቹ በቀጣይ የየትምህርት ቤቶቻቸውን መረጃዎች በስልጠናው መሰረት በሶፍትዌሩ ላይ የሚመዘገቡ ይሆናል ብለዋል፡፡

ስልጠናው ከትምህርት ሚኒስቴር በመጡ ባለሙያዎች በመሰጠት ላይ ሲገኝ በስልጠናው ላይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የICT ባለሙያዎች ፣ የሁሉም ክፍለከተሞች  የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽንና መረጃ ባለሞያዎች እንዲሁም የትምህር ቤቶች መሻሻል ቡድን መሪዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 30
  • 222
  • 1,584
  • 6,364
  • 214,625
  • 214,625