በትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም አፈጻጸምን አስመልክቶ ውይይት ተካሄደ።

by | ዜና

(ግንቦት 3 ቀን 2016 ዓ.ም) ውይይቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮና ምገባ ኤጀንሲ በጋራ የተዘጋጀ ሲሆን በመርሀ ግብሩ የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዋና እና ምክትል ርዕሳነ መምህራንን ጨምሮ የትምህርት ቤት የምገባ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሽታዬ መሀመድ በውይይቱ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ከተማ አስተዳደሩ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የመንግስት ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራምን ተግባራዊ አድርጎ ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ ገልጸው የምገባ ስርአቱ ከፍተኛ በጀት ተመድቦለት ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኝ መርሀ-ግብር እንደመሆኑ ኤጀንሲው ከትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በትምህርት ተቋማት ባደረገው ኢንስፔክሽን የአሰራር ክፍተቶች መኖራቸውን ማረጋገጡን በመጥቀስ የዛሬው ውይይት በችግሮቹ ዙሪያ በመወያየት በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት እንዲቻል ታስቦ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር በበኩላቸው የትምህርት ቤት ምገባ መርሀ ግብር የተማሪዎችን መጠነ ማቋረጥም ሆነ መጠነ መድገም በመቀነስ የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ በኩል እያበረከተ የሚገኘው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ከመሆኑ ባሻገር ለተማሪ ወላጆች እፎይታ፣ ለመጋቢ እናቶች ደግሞ የስራ እድል መፍጠር የቻለ ፕሮግራም መሆኑን ጠቁመው ከምገባ ፕሮግራሙ አፈጻጸም ጋር በተገናኘ በአንዳንድ ተቋማት የሚታዩ የአፈጻጸም ችግሮችን መቅረፍ  እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

0 Comments

SITE VISITORS

  • 0
  • 179
  • 249
  • 2,415
  • 8,967
  • 243,949
  • 243,949