የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ከአቶ ይታገሱ ካሳ ጋር በመሆን በተለያዩ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተዘዋውረው የሁለተኛውን ቀን የፈተና አጀማመር ተመልክተዋል።
ዶክተር ዘላለም ምልከታውን ባካሄዱባቸው ሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች የጸጥታ አካላትን ጨምሮ የፈተና አስፈጻሚዎች ከትላንት ጀምሮ ፈተናው ያለምንም ችግር እንዲካሄድ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበው ከነገ ጀምሮ የሚካሄደው የ6 ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናም ያለምንም የጸጥታም ሆነ ሌላ ችግር ተካሂዶ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካል በተመሳሳይ ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዘንድሮ በ182 የፈተና ጣቢያዎች 75,100 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውን ቀደም ሲል መግለጻችን የሚታወቅ ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ ከነገ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚሰጥ ይሆናል።
0 Comments