በትላንትናው እለት የተጀመረው የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች ግምገማዊ ስልጠና ተጠናቀቀ።

by | ዜና

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 5 ፣ 2015 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) ግምገማዊ ስልጠናው የትምህርት ሴክተሩን የ2015ዓ.ም አፈጻጸምና የ2016ዓ.ም እቅድን መሰረት አድርጎ የተካሄደ ሲሆን የመርሀ ግብሩ ተሳታፊዎች በቀረበው ሰነድ ዙሪያ ባካሄዱት የቡድን ውይይቶች ያነሱዋቸውን የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች በጽሁፍና በክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ኃላፊዎች አማካይነት አቅርበው በቢሮ አመራሮች ምላሽ ተሰቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር በመርሀ ግብሩ እንዳስታወቁት በዘንድሮው የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በቀን ተማሪዎች አበረታች ውጤት የተመዘገበ ቢሆንም የማታ ተማሪዎችን ከማብቃት አኳያ የታዩ ችግሮች ባስቸኩዋይ ሊስተካከሉ እንደሚገባ ገልጸው ትምህርት ቤቶች የ2016ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ መርሀ ግብርን በሁሉም የትምህርት እርከኖች ቢሮው በሚልከው ፎርም መሰረት ማካሄድ እንደሚገባቸው አስረድተዋል።

አዲሱን ስርአተ ትምህርት መሰረት አድርጎ በተጀመሩ አዳዲስ የትምህርት አይነቶች ለሚያስተምሩ መምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እንደሚሰጡ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አሊ ከማል ጠቅሰው የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻል የትምህርት አመራሩ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ አመራሩ ኃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ እንደሚገባ አስረድተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በግምገማዊ ስልጠናው ባስተላለፉት መልዕክት  ዘንድሮ የተካሄደው የትምህርት አመራሩ ግምገማዊ ስልጠና ቀድሞ ከነበረው አንጻር በጥብቅ ዲስፕሊን የተካሄደ መሆኑን በመግለጽ የትምህርት ስርአቱ ውጤታማ እንዲሆን አዲስ መዋቅር እየተጠና እንደሚገኝ እና በዋናነትም የተማሪዎችና የመምህራንን የዲሲፒሊን ችግሮች የሚቀርፍ መመሪያ እየተዘጋጀ እንደሚገኝ ጠቁመው በቅርቡ የተጀመረው የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ እንዲችል አመራሩ ሚናውን በአግባቡ ሊወጣ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ዶክተር ዘላለም አክለውም በ2016ዓ.ም የመማር ማስተማር ስርአቱ ውጤታማ እንዲሆን የትምህርት ቁሳቁሶችንም ሆነ የመማሪያ መጽሀፎችን ለማቅረብ የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው በትምህርት ተቋማት አከባቢ የሚገኙ አዋኪ ጉዳዮችን ማስወገድ እንዲቻል ችግሮቹን በመለየት እንዲወገዱ ማድረግ እንደሚገባ አስረድተዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 27
  • 222
  • 1,581
  • 6,361
  • 214,622
  • 214,622