በትላንትናው እለት በመንግስት ትምህርት ቤቶች የተጀመረው የ2016 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡

by | ዜና

አዲስ አበባ ነሀሴ 24 /2015 ዓ.ም  የዘንድሮው ምዝገባ የኢ-ስኩል ሲስተም አካል በሆነው ስኩል ሪጅስትሬሽን ሲስተም መሰረት በተዘጋጀ የመመዝገቢያ ፎርማት እየተካሄደ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮምኒኬሽን ቡድን መሪ አቶ ታዬ ወልደኪዳን ገልጸው ፎርማቱ የተማሪዎችን እና ወላጆችን አጠቃላይ መረጃዎችን አካቶ መዘጋጀቱንም አስታውቀዋል፡፡

ቡድን መሪው አክለውም በስኩል ሪጅስትሬሽን ሲስተም በተዘጋጀው ፎርማት ምዝገባው ተካሂዶ እንደተጠናቀቀ  አጠቃላይ መረጃው ከተማሪዎች ፎቶ ግራፍ ጋር ወደ  ኢ-ስኩል ሲስተም እንደሚጫን(apload እንደሚደረግ)  ጠቁመው ይህም ከዚህ በፊት ከተማሪዎች ቁጥርም ሆነ ሌሎች ከመረጃ ጋር በተገናኘ የሚስተዋሉ ችግሮችን እንደሚቀርፍ አስገንዝበዋል፡፡

ምዝገባው ከሚካሄድባቸው ትምህርት ቤቶች መካከል ጉለሌ ክፍለከተማ የሚገኙት ፀሀይ ጮራ እና ድል በትግል አንደኛ ደረጃ እንዲሁም እንጦጦ አምባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ምዝገባው ከቢሮ በተላከው የበስኩል ሪጅስትሬሽን ሲስተም መሰረት ያለምንም ችግር እየተካሄ እንደሚገኝ የትምህርት ቤቶቹ ርዕሳነ መምህራን ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል፡፡

              

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 308
  • 374
  • 4,289
  • 15,619
  • 98,485
  • 98,485