(ጥቅምት 17/2017ዓ.ም) ስልጠናው በቢሮው የልዩ ፍላጎት ፣የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት የተዘጋጀ ሲሆን በመርሀ ግብሩ የተፋጠነ ትምህርት ከሚሰጥባቸው ክፍለ ከተሞች የተመረጡ የዘርፉ ቡድን መሪዎችና የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ባለሙያዎች ፣የወረዳ ባለሙያዎች እንዲሁም ትምህርቱን የሚያስተምሩ አመቻቾች ተሳታፊ ሆነዋል።
ከተማ አስተዳደሩ በመደበኛው ፕሮግራም ለበርካታ ዜጎች ትምህርትን በፍትሀዊነት ተደራሽ በማድረግ ላይ የሚገኝ ቢሆንም አሁንም ቢሆን ቁጥራቸው ቀላል ያልሆነ ዜጎች በተለያዩ ምክንያቶች የመደበኛ ትምህርት አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸውን የልዩ ፍላጎት፣ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ጌታቸው በላይነህ ጠቁመው እነዚህን ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ከመደበኛው ፕሮግራም ውጪ በሆነው የተፋጠነ የትምህርት መርሀግብር የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን አመላክተዋል።
አቶ ጌታቸው አያይዘውም የተፋጠነ የትምህርት ፕሮግራም እድሜያቸው ከ9 እስከ 14 አመት የሆኑ ህጻናትና ወጣቶች የትምህርት አገልግሎት አግኝተው ከእኩዮቻቸው እኩል ዕውቀት እንዲጨብጡ የሚያስችል መርሀግብር መሆኑን ገልጸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ፕሮግራሙ በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ እንዲሆን ታስቦ መዘጋጀቱን አስገንዝበዋል።
ስልጠናው ከተፋጠነ የትምህርት ፕሮግራም ጋር በተገናኘ ለበርካታ አመታት የማሰልጠን ልምድ ባላቸው ምሁራን መሰጠቱን የቢሮው የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ባለሙያ አቶ አበበ ዘነበ ጠቁመው በቀጣይ የፕሮግራሙን አተገባበር በተመለከተ በየክፍለ ከተማው የድጋፍና ክትትል ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
በተፋጠነ የትምህርት መርሀግብር(accelerated learning program) ጽንሰ ሐሳብ ፣በትምህርቱ የማስተማር ሥነ ዘዴ እና በተጨመቀው ስርአተ ትምህርት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
0 Comments