በተጨማሪነት በመሰራጨት ላይ የሚገኙ መጻሕፍትን በተመለከተ ፡- ማስታወቂያ ለግል ትምህርት ቤቶች

by | ዜና

(አዲስ አበባ 14/1/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለ2016 የትምህርት ዘመን ቅድመ ዝግጅቶችን በማድረግ የመማር ማስተማር ስራው በከተማ አስተዳደሩ ከመስከረም 7/2016 ዓ.ም ጀምሮ አንዲካሄድ እያደረገ ይገኛል፡፡

በቅድመ ዝግጅት ስራው ውስጥ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው ለትምህርት ዘመኑ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ማሟላት ሲሆን  ከነዚህ ግብዓቶች መካከል በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የታተሙ  የተማሪ መማሪያ መጻሕፍትና የመምህሩ መምሪያዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በመሆኑም ግብአቶቹ እንዲሟሉ በማድረግ  ለግል  ትምህርት ተቋማት  በሚኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሰራጭ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡

ከዚህ ቀደም ለግል ትምህርት ቤቶች በሚኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመሰራጨት ላይ እንደሚገኙ ከተገለፁት   የመማሪያ  መጻሕፍትና የመምህሩ መምሪያ  በተጨማሪ   የ1ኛ ፣ የ2ኛ እና  የ8ኛ ክፍል የሒሳብ  ትምህርት የመምህሩ መምራያ እና የ8ኛ ክፍል የአይቲ ትምህርት  የመምህሩ  መምሪያም  በመሰራጨት ላይ እንደሚገኝ እናሳውቃለን፡፡  በምትመጡበት ጊዜ ከዚህ ቀደም ለክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ያስገባችሁትን ፍላጎት ዝርዝር በመያዝና  በክፍለ ከተማው ት/ጽ/ቤት ማህተም በማረጋገጥ ይዛችሁ መገኘት አለባችሁ፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 0
  • 175
  • 2,114
  • 9,135
  • 234,185
  • 234,185