በተማሪዎች ደንብ ልብስ ጥራት ቁጥጥር እና ስርጭት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት ተጀመረ፡፡

by | ዜና

(አዲስ አበባ 11/1/2016 ዓ.ም) ስልጠናው በሁሉም ክፍለከተሞች ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ የተማሪ ምገባና ንብረት ክፍል ባለሙያዎች እንዲሁም ለክፍለ ከተማ የትምህርት ቤት መሻሻል ቡድን መሪዎችና አስተባባሪዎችን ጨምሮ ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ለመጡ የጥራት ተቆጣጣሪዎች የሚሰጥ ሲሆን ስልጠናውም ከኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ ኢንስቲቲዩት በመጡ አሰልጣኞች በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

ስልጠናው በዋናነት ሰልጣኞቹ ለተማሪዎች የተዘጋጀው ደንብ ልብስ ጥራቱን በጠበቀና የተማሪዎችን ሳይዝ መሰረት አድርጎ በተዘጋጀው ስፔክ መሰረት መቅረቡን እያረጋገጡ እንዲረከቡ ታስቦ መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት መሻሻል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቀጸላ ፍቅረማርያም አስታውቀዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለውም በስልጠናው ከደንብ ልብስ ባሻገር ለ2016ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለተማሪዎች የሚሰራጩት የመማሪያ ደብተሮች በስፔኩ መሰረት መዘጋጀታቸውን እያረጋግዙ ለተማሪዎች ማሰራጨት እንዲችሉ የሚያስችላቸውን ግንዛቤ እንደሚያገኙም አስታውቀዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 0
  • 175
  • 2,114
  • 9,135
  • 234,185
  • 234,185