በቦሌ ቡልቡላ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የመስክ ምልከታ ተደረገ ::

by | ዜና

(አዲስ አበባ ህዳር 27 ቀን 2016 ዓ.ም)  በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እየተሰሩ ያሉትን ሥራዎች ምልከታ ለማካሄድ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ እየተደረገ ያለው የመስክ ጉብኝት  ዛሬም ቀጥሎ ውሏል ::

የመስክ ምልከታው በቦሌ ቡልቡላ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተደረገ ሲሆን  የአጥር ፣ የስታዲየምና የቤተ ሙከራ ክፍሎች ግንባታ ያለበት ደረጃ ፣ የሴት ተማሪዎች መፀዳጃ ክፍሎች ሥራና የመማሪያ ክፍሎች እድሳት ስራዎች ያሉበት ደረጃ በምልከታው ውስጥ ተካቷል ::

እስካሁን ከታዩ የትምህርት ለልማት ፕሮጀክት ስራዎች ውስጥ ግዙፍና ሰፊ ስራዎች የተሰሩበት ፕሮጀክት መሆኑን የገለፁት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በትምህርት ቤቱ እየተከናወኑ የሚገኙ  ሥራዎችን አድንቀው ፕሮጀክቱ በፍጥነት ተጠናቅቆ ለአገልግሎት እንዲውል  አቅጣጫ አስቀምጠዋል :: ዶክተር ዘላለም አያይዘውም በጊቢው የሚታየውን  የውሃ እጥረት ችግር ለመቅረፍ  የጉድጓድ ውሃ ቁፋሮና የማስፋፊያ  ስራዎች ከውሃና ፍሳሽ ቢሮ ጋር በጋራ የሚሰራ መሆኑን ገልፀዋል ::

በመስክ ምልከታው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ  ወ/ሮ ዓለምፀሀይ ሽፈራው  ፣ የትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት  ፣ የቦሌ ቡልቡላ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ተሾመ ባቱ ተገናኝተዋል ::

ፕሮጀክቱ ከ146 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ወጪ እየተገነባ ያለ መሆኑንና አጠቃላይ ወጪው በአርባ ምንጭ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ባለቤት የሚሽፈን መሆኑን ከትምህርት ቤቱ የተገኝ መረጃ ያሳያል ::

 

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 27
  • 222
  • 1,581
  • 6,361
  • 214,622
  • 214,622