በቅድመ አንደኛ ደረጃ ስርአተ ትምህርት አተገባበርና በትምህርት መርጃ መሳሪያ አዘገጃጀት ዙሪያ ለሁለት ቀን የሚቆይ ስልጠና መስጠት ተጀመረ።

by | ዜና

(ግንቦት 2 ቀን 2016 ዓ.ም) መርሀ ግብሩ  በቢሮው የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት አማካይነት የተዘጋጀ ሲሆን በስልጠናው የሁሉም ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተባባሪዎችን ጨምሮ የክፍለ ከተማ ዘርፈ ብዙ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ በላይነሽ የሻው በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ህጻናት በአካል፣አዕምሮና በስነ ልቦና ዳብረው ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ዝግጁ የሚሆኑበት የትምህርት ደረጃ እንደመሆኑ የስልጠናው ተሳታፊዎች ከትምህርቱ አተገባበር ጋር በተገናኘ በቂ ግንዛቤ ይዘው ወደተግባር እንዲገቡ ለማስቻል ታስቦ ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ዳይሬክተሯ አክለውም በአዲሱ ስርአተ ትምህርት በተቀመጠው መሰረት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት በጫወታ የማስተማር ስነ ዘዴ ተግባራዊ የሚሆንበት እንደመሆኑ ከአተገባበሩ ጋር በተገናኘ በቢሮው የስርአተ ትምህርት ባለሙያዎች ስልጠና እንደሚሰጥ ገልጸው ከማስተማሪያ መርጃ መሳሪያ አዘገጃጀትና አተገባበር ጋር በተገናኘም በዘርፉ ልምድ ባላቸው ባለሙያ በተግባር የተደገፈ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑንም አስታውቀዋል።

0 Comments

SITE VISITORS

  • 0
  • 184
  • 249
  • 2,420
  • 8,972
  • 243,954
  • 243,954