በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በአዲስ ምዕራፍ ት/ቤት ለ8 ወር የስካውት ስልጠና ሲሰለጥኑ የነበሩ 30 ተማሪዎች የኢትዮጵያ  እስካውት ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ኮሚሽነር ሻምበል ጳዉሎስ ወ/ገብርኤል ፣ የተማሪ ወላጆች ፣ መምህራንና ተማሪዎች በተገኙበት  ተመርቀዋል።

የስካውት ዓላማና ተግባር የሚያተኩረው ከታዳጊ ሕፃናት አንስቶ እሰከ ወጣቶች ድረስ ያሉ ዜጎች በሚሰጣቸው ስካውታዊ ትምህርት በአካል ዳብረው ፣ በአእምሮ ልቀው፣ በመንፈስ ጠንክረው፣ ታዛዥ፣ ታማኝ፣ ትሁት፣ ቅን፣ ሰው አክባሪዎች፣ ስራ ወዳዶች፣ ራሳችውን፣ ወገናችውንና ሀገራቸውን ማገልገል የሚችሉ፣ ሀገራቸውን የሚወዱና  በራሳቸው የሚተማመኑ ዜጎችን ማፍራት እንደሆነ በምረቃ ስነ-ስርስርዓቱ ላይ ተጠቅሳል፡፡ በተጨማሪም የስካውት ተግባር ወጣቶች ሁለንተናዊ ስብዕናቸው የተሟላ ሀገር ገንቢ ዜጋ እንዲሆኑ፣በተጨማሪም በሥነ ምግባር የታነጹና በራስ የመተማመን ባህሪ የተላበሱ፣ ለሀገርና ለወገን ተገቢውን አገልግሎት በነፃ መስጠት የሚችሉ ንቁ ዜጎችን ማፍራት እንዲቻል መልካም ሁኔታዎችን የሚያመቻች  መሆኑም በእስካውት ስራ አስፈፃሚው  ተመላክቷል ፡፡