በቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

by | ዜና

(ህዳር 4/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትምህርት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ስለቀዳማይ ልጅነት ምንነት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

ስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለሚገኙ ለዓላማ ፈጻሚ የስራ ክፍሎች የተሰጠ ሲሆን የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትምህርት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወይዘሮ በላይነሽ የሻው ቀዳማይ ልጅነት ላይ መስራት ሀገር ላይ መስራት መሆኑን  ባስተላለፉት መልዕክት ላይ ገልፀዋል፡፡

ስልጠናዉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም አስተባባሪ ታቦር ገ/መድን (ዶ/ር)እና የፕሮጀክት ፅ/ቤት  አስተባባሪ  በሆኑት ወ/ሮ ወይንሸት ቀረብህ  የተሰጠ ሲሆን  ተሳታፊዎች  ስለቀዳማይ ልጅነት ምንነትና አፈጻጸ  ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸዉ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን በመድረኩ የተመላከተ ሲሆን ይህ ፕሮግራም የህጻናት ዕድገት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ መሆኑን ተገልጻል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 204
  • 158
  • 7,077
  • 31,330
  • 147,474
  • 147,474