በሰላማዊ መማር ማስተማር ዙሪያ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ የመንግስትና የግል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን ጋር ውይይት ተካሄደ።

by | ዜና

(ህዳር 21/2016 ዓ.ም) ውይይቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር  ቢሮ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን በውይይቱ በሰላማዊ የመማር ማስተማር አተገባበርን በተመለከተ የተዘጋጀ የመወያያ ሰነድ በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ በአቶ ማስረሻ ሀብቴ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በመርሀ-ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት በትምህርት ተቋማት ከጸጥታ ጋር የሚስተዋሉ አዝማሚያዎች የመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ችግር እንዳይፈጥሩም ሆነ በተቋማቱ የሚገኙ ንብረቶች ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ በአመቱ መጀመሪያ ቢሮው ከሰላምና ጸጥታ ቢሮ ጋር በመሆን ባለድርሻ አካላትን በማወያየት ወደ መማር ማስተማር ስራ መግባቱን አስታውቀዋል።

ዶክተር ዘላለም አክለውም ትምህርት ቤቶች ከማንኛውም የፖለቲካም ሆነ ሀይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች ነጻ ሆነው መደበኛ የመማር ማስተማር ስራቸውን በአግባቡ ተግባራዊ ማድረግ እንዲችሉ ከባለድርሻ አካላት ጋር በየደረጃው ውይይት እንደሚካሄድ ጠቁመው በትምህርት ተቋማት የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮች ከመንግስት ትምህርት ቤቶች ባሻገር በአንዳንድ በግል ትምህርት ቤቶችም እየተስተዋሉ በመሆናቸው የትምህርት ቤት ባለቤቶችና አመራሮች ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው መንቀሳቀስ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ በበኩላቸው በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ የጸጥታ ችግሮችን ለመፍጠር የሚፈልጉ አካላት ትምህርት ቤቶች ዋነኛ የብጥብጥ ማዕከል እንዲሆኑ ትኩረት አድርገው እንደሚንቀሳቀሱ ጠቁመው ችግሩ የመማር ማስተማር ስራውን እንዳያውክ የትምህርት ማህበረ ሰቡ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው ማድረግ እንደሚገባ በመግልጽ የጸጥታው ክፍልም በጉዳዩ ተሳታፊ የሚሆኑ አካላትን በህግ ተጠያቂ የማድረግ ኃላፊነቱን በአግባቡ የሚወጣ መሆኑን አስታውቀዋል።

 

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 2
  • 52
  • 222
  • 1,606
  • 6,386
  • 214,647
  • 214,647