በመልካ ዳንሴ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና በንፋስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ጉብኝት ተካሄደ።

by | ዜና

(ቀን ታህሳስ 17/2016 ዓ.ም) በንፋስ ሰልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በሚገኘው  መልካ ዳንሴ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና በንፋስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ጉብኝት ተካሄደ፡፡

በጉብኝቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ  ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ታጋይቱ አባቡ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ  አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ ፣ የንፋስ ሰልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ብርሀኑ አበራ  ፣ የንፋስ ሰልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አለልኝ ወንዴ ፣ የንፋስ ሰልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ በላይ ነጋሽ፣ መምህራንና ርዕሳነ መምህራን ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በጉብኝቱ የመልካ ዳንሴ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመማር መስተማር ስራው የትምህርት ቤቱ የምድረ ግቢ ምቹነት ፣ የትምህርት ግብአቶች አቅርቦት ያለበት ሁኔታ በአጠቃላይ የትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማር ስራ  ዳሰሳ የተካሄደ ሲሆን በትምህርት ተቋሙ የሚሰጠውን ትምህርት ውጤታማ ለማድረግ መሰራት በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ተቀምጣል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 27
  • 222
  • 1,581
  • 6,361
  • 214,622
  • 214,622