በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት ፣ ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የመስክ ምልከታ አካሄደ።

by | ዜና

(ህዳር 12 ቀን 2016 ዓ.ም) የመስክ ምልከታው ከቢሮው በተጨማሪ በተመረጡ ክፍለ ከተሞችና ትምህርት ቤቶች የሚካሄድ መሆኑን የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ቤተልሔም ላቀው ጠቁመው የመስክ ምልከታው በዋናነት ከ2016 ዓ.ም እቅድ በመነሳት በተቋማቱ በ1ኛ ሩብ አመት የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት አድርጎ የሚካሄድ መሆኑን በመጥቀስ በትምህርት ቤቶች የሚደረገውን ምልከታ መሰረት በማድረግ በትምህርት ቢሮ ዳግም በሚካሄድ ውይይት ግብረ  መልስ የሚሰጥ መሆኑንም ገልጸዋል።

በመርሀ – ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር በበጀት አመቱ ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ሪፖርት አቅርበው በቋሚ ኮሚቴው አባላት የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ ተሰቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከቋሚ ኮሚቴ አባላት ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን ቋሚ ኮሚቴው ከቢሮ ጀምሮ በትምህርት ቤቶች በመገኘት የመስክ ምልከታ ማካሄዱ በቀጣይ በትምህርት ልማት ስራው የምናከናውናቸውን ተግባራት ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ አቅም እንደሚሆን አስታውቀዋል።

ዶክተር ዘላለም አክለውም ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት መዋቅራዊ ትስስር በመፍጠር የትምህርት ስራው ያለበት ሁኔታ እንደሚገመገም ገልጸው የግል ትምህርት ቤቶች ስርዓተ ትምህርቱን በአግባቡ ተግባራዊ እንዲያደርጉም ሆነ ከክፍያ ስርዓት ጋር በተገናኘ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመቅረፍ ቢሮው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ጋር በጋራ እየሰራ እንደሚገኝም አስገንዝበዋል።

 

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 1
  • 58
  • 222
  • 1,612
  • 6,392
  • 214,653
  • 214,653