(ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም) በሒሳብና እንግሊዘኛ የትምህርት አይነቶች ተማሪዎችን ውጤታማ ለማድረግ የተዘጋጀውን ስትራቴጂክ እቅድ አፈጻጸምን አስመልክቶ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተካሄደ የመጀመሪያ ዙር ድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ ውጤት ላይ እንዲሁም በሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት በሪፎርም ሥራዎች ላይ በሁሉም ክፍለ ከተሞችና በቢሮው ዳይሬክቶሬቶች ባደረገው 1ኛ ሩብ ዓመት ክትትልና ድጋፍ ማጠቃለያ ሪፖርት ላይ ውይይት ተደርጓል::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በውይይቱ ላይ እንዳሉት በሂሳብና እንግሊዘኛ ትምህርቶች ላይ የተሰበሰቡ የድጋፍና ክትትል ውጤቶች መሰረት በማድረግ የትምህርት አመራሩ ለስትራቴጂው ውጤታማነትና ለተማሪዎች ውጤት መላቅ በጥብቅ ዲስፕሊን ተግባራትን እንዲመሩና የመማር ማስተማር ሂደቱ የተማሪን ውጤት በሚያጎለብት መልኩ እንዲሆን አሳስበዋል::
በተያያዘም በ2017 ዓ.ም መጀመሪያ ሩብ ዓመት ሪፎርም ሥራዎች ላይ የተደረገ ክትትልና ድጋፍን መሰረት በማድረግ በተሰጡ ግብረ መልሶችን ማስተካከል እንደሚገባ በመጥቀስ በቀጣይም በወረዳና ትምህርት ቤቶች ላይ ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወ /ሮ አበበች ነጋሽ በበኩላቸው የተሰጡ ግብረ መልስ አስተማሪ ናቸዉ በሚል ተወስዶ ችግሮችን ለመቅረፍ በትጋት እንዲሰራ ጠይቀዋል ::
በውይይቱ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፣ ምክትል ቢሮ ሃላፊዎች ፣ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ፣ የክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊዎችና አስተባባሪዎች ተሳትፈዋል ::
በሒሳብና እንግሊዘኛ የትምህርት አይነቶች ተማሪዎችን ውጤት ለማላቅ የተዘጋጀውን ስትራቴጂ እቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ በክፍለ ከተሞች በተካሄደ የመጀመሪያ ዙር የክትትልና ድጋፍ ግብረ መልስ ውጤት ላይ ውይይት ተካሄደ።
0 Comments