በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት በስርአተ ትምህርት ትግበራና ክትትል ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት ያደረገ ከተማ አቀፍ የልምድ ልውውጥ መርሀ ግብር ተካሄደ።

by | ዜና

(ቀን ሚያዚያ 4/ 2016 ዓ.ም) በልምድ ልውውጡ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የሁለቱ ስርአተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎችን ጨምሮ የቢሮው የስርአተ ትምህርት ማበልጸግና ትግበራ ባለሙያዎች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በመርሀ ግብሩ የልደታ ክፍለ ከተማ የስርአተ ትምህርት ትግበራና ክትትል አስተባባሪ አቶ ገዳ ሞሲሳ በጽህፈት ቤቱ በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተካሂዷል።

                 

የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰኢድ አሊ በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ትምህርት ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደመሆኑ መንግስት ለብዝሀነት እና ሀገር በቀል እውቀቶች ትኩረት የሰጠ አዲስ ስርአተ ትምህርት አዘጋጅቶ ወደ ተግባር መግባቱን ገልጸው የክፍለ ከተማው አ ተዳደር ለስርአተ ትምህርቱ ተግባራዊነትም ሆነ ለአጠቃላይ የትምህርት ልማት ስራው ውጤታማነት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስገንዝበዋል።

               

የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ እጅጋየሁ አድማሱ በበኩላቸው ጽህፈት ቤቱ ስርአተ ትምህርቱን በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እንዲሻሻል ከባለድርሻ አካላት ጋር ባከናወናቸው ተግባራት ውጤታማ  መሆኑን ጠቁመው የዛሬው መርሀ ግብር እርስ በእርስ ልምድ በመለዋወጥ በቀጣይ ተቀራራቢ አፈጻጸም ለማስመዝገብ የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑንም አስታውቀዋል።

                   

ክፍለ ከተማው በበጀት አመቱ ግማሽ አመት ከሁለቱ ስርአተ ትምህርቶች አተገባበር ጋር በተገናኘ ውጤታማ ከሆኑ ክፍለ ከተሞች መካከል ግንባር ቀደም በመሆኑ የልምድ ልውውጥ መርሀ ግብሩ መዘጋጀቱን የቢሮው የስርአተ ትምህርት ማበልጸግና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ታለማ እና የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ማበልጸግና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሮቢ ዋሚ ገልጸው የልምድ ልውውጡ ተሳታፊዎችም ጽህፈት ቤቱ ስርአተ ትምህርቱን በአግባቡ ተግባራዊ ለማድረግ ያከናወናቸውን ተግባራት መ ሰረት በማድረግ በየክፍለ ከተሞቻቸው ውጤታማ ስራ መስራት የሚጠበቅባቸው መሆኑንም አስገንዝበዋል።

0 Comments

SITE VISITORS

  • 0
  • 187
  • 249
  • 2,423
  • 8,975
  • 243,957
  • 243,957