(ታህሳስ 16/2017 ዓ.ም) በውይይቱ በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተደረገው ድጋፍና ክትትል የተሳተፉ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ቡድን መሪዎችና የቢሮው የዘርፉ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ በላይነሽ የሻው ድጋፍና ክትትሉ በሁሉም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሁለተኛ ሩብ አመት በዘርፈ ብዙ ጉዳዮች የተከናወኑ ተግባራት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ በማየት በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት እንዲቻል ታስቦ መካሄዱን ገልጸው በድጋፍና ክትትሉ የቀረቡ ግብረ መልሶችን መሰረት በማድረግ በቀጣይ የተሻለ ስራ የሚሰራ መሆኑን አመላክተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ቡድን መሪ አቶ ይልማ ተሾመ በሁለተኛ ሩብ አመት በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተደራጁ የስርአተ ፆታ እና የኤች አይ ቪ ኤድስ ክበባት እንቅስቃሴን ጨምሮ በሌሎች የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ከተከናወኑ ተግባራት ጋር በተገናኘ በግብረ መልሱ የቀረቡ ነጥቦችን በዝርዝር አቅርበው ተሳታፊዎች ውይይት አካሂደዋል።
0 Comments