ENGLISH                                                                                                                                                              የዌብሜይል     መልዕክት ይላኩልንበ”ትምህርት በቤቴ“ መርሃ ግብር ጥሩ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በ”ትምህርት በቤቴ“ መርሃ ግብር በአጭር የፅሁፍ መልእክት ለተሳተፉና ጥሩ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።በኮረና ወረርሽኝ ምክንያት በአፍሪ ሄልዝ ቴሌቪዥን ፣ በኤፍ ኤም 94.7 ሬዲዮና በሌሎች

የኢንተርኔት አማራጮች ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል እየተሰጠ ባለው ትምህርት በተለይም ደግሞ በትምህርት በቤቴ መርሃ ግብር ላይ  የተማሪዎችን ተሳትፎ ለማጠናከርና በትምህርታቸው እውቀት መገብየታቸውን ለመለካት ሲካሄድ በነበረዉ የ8455 የሽልማት መወዳደሪያ መልዕክት መላኪያ ላይ የአሸናፊ ተማሪዎች ሽልማት መርሃ ግብር ዛሬ ግንቦት 13/2012 ዓ/ም ተካሄደ፡፡

በተካሄደው መርሃ ግብር ከ7ኛ –12ኛ ክፍል ላሉ 30 አሸናፊ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው ላፕ ቶፕ ኮምፒውተር እና ለ11 ልጆቻቸዉን ለዚህ ላበቁ ቤተሰቦች የ43 ኢንች ቴሌቪዥን ሽልማት ተበርክቶላቸዋል::

በሽልማት መርሃ ግብሩ ተገኝተው ሽልማቱን ያስጀመሩትና መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ (ኢ/ር) ታከለ ኡማ እንደገለፁት አዲስ አበባን ከሚመጥን ተግባር መካከል ትውልድን በትምህርት መገንባትና ተገቢውን ተግባር በመፈፀም በትምህርት ቤቶች መካከል ያለውን ልዩነት በማስተካከል በመንግስት ትምህርት ቤት መማር ኩራት መሆኑን በስራ ማሳየት ነው ብለዋል፡፡ አክለውም ለዚህ ደግሞ በተማሪዎችና በመምህራን ላይ ኢንቨስትመንት በመጨመር በተማሪዎች አልባሳት( ዩኒፎርም ) ፣ በምገባ መርሃ ግብር ፣ በትምህርት መማሪያ ግብአቶች እና መስል የትምህርት ግብዓቶችን ለማሟላት በአዲስ መልክና ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል ፡፡ በተያዘው አመት ለ300ሺህ ተማሪዎች እየተደረገ ያለው “የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር” በቀጣዩ አመት 600 ሺህ ተማሪዎች የሚካተቱበት ይሆናል ሲሉ ኢ/ር ታከለ ኡማ ጨምረዉ ተናግረዋል።

የትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ የትምህርት መርሃ ግብሩ እንዲሳካ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ የከተማው አስተዳደር ፣ በየደረጃው ላሉ የትምህርት ቢሮ አመራሮችና የትምህርት ባለሙያዎች፣ ለአፍሪ ሄልዝ ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጆችና ባለሙያዎች እንዲሁም ለሌሎች በትምህርት ቢሮ ስም አመሰግናለሁ ብለዋል

 

ድጋሚ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ አገልግሎት ለማግኝት መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች


 • ማንነትን የሚገልጽ ህጋዊ መታወቂያ ይዞ መቅረብ
 • ባለሙያው የሚሰጠውን ቅጽ መሙላት
 • ከአንድ ዓመት ወዲህ የተነሱትን 3×4 የሆነ ፎቶ ግራፍ
 • ጠያቂው ወይም ህጋዊ ወኪል በአካል መቅረብ ይገባዋል
 • ከላይ የተገለጹት ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉ 25.00 ብር በመክፈል አገልግሎቱን ማግኘት ይቻላል

የአቻ ግመታ አገልግሎት ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች


 • የትምህርት መረጃውን በተማሩበት አገር የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቦርድ ወይም District of education /council/ በጀርባው ላይ የባለስልጣኑ ስም፣ ቲተርና ማህተም እንዲሁም በተማሩበት ሀገር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማህተምና ፊርማ የተረጋገጠ መሆን አለበት ፡፡
 • የትምህርት መረጃው ከእንግሊዘኛ ቋንቋ ውጪ የተጻፈ ከሆነ በኢትዮጵያ ህጋዊ መተርጎም ፈቃድ ባላቸው ድርጅቶች የተተረጎመና በተርጓሚው ድርጅት ማህተም የተረጋገጠ መሆን ይገባዋል ፡፡
 • በትምህርት መረጃው የፈተና ውጤቶች በፊደል ወይም በቁጥር ከተሰጡ ምን ማለት እንደሆነ አቻ መገለጫ ያለው መሆን አለበት
 • የትምህርት መረጃና የሌሎች ማስረጃዎች ዋናና አንዳንድ ፎቶ ኮፒ መቅረብ አለበት
 • መረጃ ጠያቂው ወይም ህጋዊ ወኪል በአካል መቅረብ ይኖርበታል
 • ከላይ የተገለጹት ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉ 50.00 ብር በመክፈል አገልግሎቱን ማግኘት ይቻላል ፡፡
የመም/ሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት

የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ሂደት በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ ያሉና ወደ ስርዓቱ የሚገቡ መምህራን፣ ርምመምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ሙያው የሚጠይቀውን የብቃትና የስነ ምግባር ደረጀ ያሟሉ እንዲሆኑ፣ ሥርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል ነው፡፡
…ሙሉ ጽሁፉን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ…

አገር አቀፍ የርዕሰ መምህራን ሙያዊ ብቃት ስታንዳርድ—ዳዎንሎድ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የትምህርት ቤት ሱፐርቫይዘሮች ሙያዊ ብቃት ስታንዳርድ—ዳዎንሎድ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

የFM 94.7 ያለፉ ፕሮግራሞችን ያድመጡ

ኡሁን እየተደመጠ ያለዉ :

ዕዉቀት መፅሔት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስር በየወሩ የምትታተም መፅሔት

ቅጽ 4 ቁጥር 10 የነሐሴ 2008 ዓ.ም እትም