ማስታወቂያ ለግል ትምህርት ቤቶች!

by | ዜና

(አዲስ አበባ 11/1/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለ2016 የትምህርት ዘመን ቅድመ ዝግጅቶችን በማድረግ የመማር ማስተማር ስራው በከተማ አስተዳደሩ ከመስከረም 7/2016 ዓ.ም ጀምሮ አንዲካሄድ እያደረገ ይገኛል፡፡

በቅድመ ዝግጅት ስራው ውስጥ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው ለትምህርት ዘመኑ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ማሟላት ሲሆን ከነዚህ ግብዓቶች መካከል በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የታተሙ የተማሪ መማሪያ መጻሕፍትና የመምህሩ መምሪያዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በመሆኑም ግብአቶቹ እንዲሟሉ በማድረግ ለመንግስት ትምህርት ተቋማት የተሰራጨ ሲሆን ለግል ትምህርት ተቋማትም በሚኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሰራጭ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡

የግል ትምህርት ተቋማት ሚኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምጣት በፎቶ ላይ የተዘረዘሩትን የመማሪያ መጻሕፍትንና የመምህር መምሪያን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን በምትመጡበት ጊዜ ከዚህ ቀደም ለክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ያስገባችሁትን ፍላጎት ዝርዝር በመያዝና በክፍለ ከተማው ት/ጽ/ቤት ማህተም በማረጋገጥ ሊሆን ይገባል፡፡


ከዚህም በተጨማሪ የተቀሩ መጻሕትን ስርጭት በተመለከተ በቀጣይ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡

          

መሳሰቢያ ፡- በመሰራጨት ላይ የሚገኙ መጻሕፍት ዝርዝር በፎቶ ላይ ተመላክቷል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 183
  • 249
  • 2,419
  • 8,971
  • 243,953
  • 243,953