#ማስታወቂያ፡- በረመዲያል ምደባ አዎንታዊ ድጋፍ ለምትሹ

by | ዜና

(ህዳር 6/2016 ዓ.ም) በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ እና በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል ብቻ እስከ ህዳር 12/2016 ዓ.ም እንድታመክቱ እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።

ትምህርት ሚኒስቴር በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ይፈልጋሉ ብሎ የለያቸው ጉዳዮች፦

የአካል ጉዳት ያለባቸው ተማሪዎች:- የምደባ ሲስተሙ የአካል ጉዳት ላለባቸው ተማሪዎች እኩል እድሎችን የሚሰጥ ሲሆን ልዩ ፍላጎቶቻቸውን እና ለምደባ መስፈርቶቻቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰራ ይሆናል።

አስፈላጊ ማስረጃዎች፦ ከትምህርት ቤታቸው የድጋፍ ደብዳቤ እና የአካል ጉዳት ያለበትን የሰውነት ክፍል የሚያሳይ ፎቶግራፍና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

ትክክለኛ የሕክምና ቦርድ ማስረጃዎች፡- በምደባ ወቅት የጤና ችግር ኖሮባቸው ትክክለኛ የሕክምና ማስረጃ ላላቸው ተማሪዎች ምደባው በተለየ መልኩ ሊታይ ይችላል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 0
  • 175
  • 2,114
  • 9,135
  • 234,185
  • 234,185