አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 9 ፣ 2015 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ አጠቃላይ የቢሮው ሰራተኞች በተገኙበት ውይይት አካሄደ፡፡
ውይይቱ በዋናነት ሰሞኑን በአማራ ክልል በተከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት የተፈጠሩ ችግርችን እና ችግሮቹን ለመፍታት መንግስት እየተከተለ ያለውን አሰራር መሰረት አድርጎ የተካሄደ ሲሆን የቢሮው ሰራተኞችም በቀረበው የመወያያ ሰነድ ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶችን አንስተው ከመድረክ ምላሽ ተሰቱዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በውይይቱ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት መንግስት በጽኑ መሰረት ላይ የቆመች ጠንካራ ሀገር ለመገንባት የሚያከናውናቸው ተግባራት የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ እንዳይችል ሂደቱን የሚያስተጉዋግሉ የተለያዩ አካላት በየአከባቢው ችግር በመፍጠር ላይ እንደሚገኙ ገልጸው ሰሞኑን በአማራ ክልል የተፈጠረው የጸጥታ ችግርም እነዚሁ አካላት የክልሉን ሰላምና ጸጥታ በማወክ እኩይ አላማቸውን ለማስፈጸም የፈጠሩት እንደመሆኑ መንግስት ክልሉን ወደተረጋጋ ሁኔታ ለመመለስ የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን አስረድተዋል፡፡
ዶክተር ዘላለም አክለውም መደማመጥ መከባበር እና በሀሳብ ብዝሃነት ማመን የሰላም መሰረቶች በመሆናቸው ሁሌም ቢሆን አጥብቀን ልንይዛቸው ይገባል ያሉ ሲሆን የዛሬው ውይይት በሁሉም መስሪያ ቤቶች እየተካሄደ እንደሚገኝ ጠቁመው የትምህርት ቢሮ ሰራተኞችም መንግስት የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጁን ዶክተር ዘላለም አክለውም መደማመጥ መከባበር እና በሀሳብ ብዝሃነት ማመን የሰላም መሰረቶች በመሆናቸው ሁሌም ቢሆን አጥብቀን ልንይዛቸው ይገባል ያሉ ሲሆን የዛሬው ውይይት በሁሉም መስሪያ ቤቶች እየተካሄደ እንደሚገኝ ጠቁመው የትምህርት ቢሮ ሰራተኞችም መንግስት የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጁን ያወጀው ክልሉን ወደተሻለ የሰላምና ጸጥታ ሁኔታ ለመመለስ በማሰብ መሆኑን በመረዳት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣት እንደሚባቸው አስገንዝበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ዑመር በበኩላቸው በአማራ ክልል የተፈጠረው የፀጥታ ችግር በክልሉ የተለያዩ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራዎችን ማድረሱን ጠቁመው ህብረተሰቡ መንግሰት በክልሉ የሚነሱ ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑን በመገንዘብ የትኛውንም ጥያቄ በሰላምና ህጋዊ በሆነ መንገድ ማቅረብ እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡
0 Comments