ለ1ኛ እና ለ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለዋና እና ለምክትል ርዕሰ መምህርነት ለመወዳደር ለተመዘገቡ ተወዳዳሪዎች በከተማ ደረጃ የተዘጋጀ የፅሁፍ ፈተና ተሰጠ።

by | ዜና

(አዲስ አበባ ታህሳስ 6/2016 ዓ.ም)   የፈተና ሂደቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት በሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ተዘዋውረዉ ተመልክተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ውድድሩ በወረዳና በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚካሄድ መሆኑን ጠቅሰው የፅሁፍ ፈተናዉን ገለልተኛ በሆነ አካል በከተማ ደረጃ  መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡  ሀላፊዉ አክለዉም በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ የ1ኛ እና የ2ኛ ደረጃ የመንግስት  ት/ቤቶችን ለመምራት የሚፈለገዉን እውቀት ብቃትና ክህሎት ያላቸዉን አመራሮች በውድድር ለመመደብ ፈተናዉ ያግዛል ብለዋል፡፡ ፈተናው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ፋይዳዉ የጎላ መሆኑንና 4335 ተወዳዳሪዎች በአራት የመፈተኛ ጣቢያዎች ፈተናዉ የተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ በበኩላቸዉ የከተማ አስተዳደሩ መምህራን ማህበር በገለልተኝነት በተዘጋጀዉ ፈተና ላይ የተሳተፈ መሆኑን በመግለጽ ማህበሩ በወረዳና በክፍለ ከተማ ደረጃ በሚካሄደዉ ውድድርም የአብይና የንዑስ ኮሚቴ አባል በመሆን እየሰራ መሆኑን ተናግረል፡፡

ፈተናዉ በዳግማዊ ሚኒሊክ ፣ በመድሃኒያለም ፣ በኮከበ ጽባህና በፍሬህይወት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የፈተና መስጫ ጣቢያዎች  ላይ ተሰጥቷል፡፡

 

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 30
  • 222
  • 1,584
  • 6,364
  • 214,625
  • 214,625