ለፋና 02 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ የሚሆን የG+4 ህንጻ መሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ፡፡

by | ዜና

(ህዳር 6/2016 ዓ.ም) በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ጀሞ አካባቢ ለሚገኘው ፋና 02 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመማሪያ ክፍል ማስፋፍያ የሚሆን  የG+4 ህንጻ መሰረተ ድንጋይ ተቀምጧል::

                 

መሰረተ ድንጋዩን ያስቀመጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱና የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ብርሃኑ አበራ ሲሆኑ ሌሎች የክፍለ ከተማ አመራሮችና የሀገር ሽማግሌዎች በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

በመርሀ-ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ  የማስፋፊያ ህንፃው ለአካባቢው ማህበረሰብ እጅግ አስፈላጊና አንገብጋቢ ነው  ያሉ ሲሆን ትምህርት ቤቱ ሌሎችም መሰረተ ልማቶች እንደሚያስፈልጉት  በመጥቀስ የሚታዩ ማነቆዎችን  ፈቶ ለትውልድ መገንብያ ብቁ ማድረግ ይገባል ብለዋል። ገንባታው በተቀመጠለት በ90 ቀን ውስጥ መጠናቀቅ እንደሚገባውም አሳስበዋል::

                               

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ በበኩላቸው የህዝቡን መሰረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን በመጥቀስ ከነዚህ ስራዎች መካከል አንዱ ትምህርት ልማት ስራ መሆኑን ጠቁመዋል። አቶ ብርሃኑ አክለውም በተቀናጀ ድጋፍና ክትትል ትምህርት ቤቱን በ3 ወራት ለማጠናቀቅ አስተዳደሩ በቁርጠኝነት ይሰራል ሲሉ ተናግረዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 0
  • 175
  • 2,114
  • 9,135
  • 234,185
  • 234,185