(ጥቅምት 20/2017 ዓ.ም) ስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት እና ሲስተሙን ባለማው ትሪያ ትሬዲንግ በተሰኘው ድርጅት በጋራ የተሰጠ ሲሆን በቢሮው የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን የሶፍት ዌርና ዳታ ማዕከል ቡድን መሪ ወይዘሮ ሰላም ተስፋዬ አማካይነት በሲስተሙ ስለተካተቱ ስድስት ሞጁሎች በዝርዝር ስልጠና ተሰቱዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ ስልጠናው በዋናነት በሲስተሙ ከተካተቱ ሞጅሎች መካከል ከሱፐርቫይዘሮች ተግባር ጋር በቀጥታ በሚገናኙ ሞጁሎች ዙሪያ በቂ ግንዛቤ በመፍጠር በትምህርትቤቶች ተገቢውን የድጋፍና ክትትል ስራ መስራት እንዲችሉ ታስቦ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።
ዳይሬክተሩ አያይዘውም ቀደም ሲል ለቢሮው የስርአተ ትምህርት ባለሙያዎቹ ተመሳሳይ ስልጠና መሰጠቱን ጠቁመው በቀጣይ በየደረጃው ለሚገኙ ለክፍለከተማም ሆነ ለክላስተር ሱፐርቫይዘሮች በኢ- ስኩል ሲስተም አተገባበር ዙሪያ ተመሳሳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
0 Comments