ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 በሚገኘው ዱዱ ቢሳ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚማሩ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።

by | ዜና

(ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም) ድጋፉ በትምህርት ቤቱ ለሚማሩ ተማሪዎች በቻይናው ፋውንዴሽን ፎር ሩራል ዴቭሎፕመንት አማካይነት የተደረገ ሲሆን ድጋፉ በክፍለ ከተማው ለሚገኙ ሌሎች ትምህርት ቤቶችም እንደሚውልም በርክክብ መርሀ ግብሩ ተገልጿል።

የቻይናው ፋውንዴሽን ፎር ሩራል ዴቭሎፕመንት ፕሮግራም ማኔጀር ሚስ ሾው በርክክብ መርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ፋውንዴሽኑ ከ2015ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ፖንዳ ፓክ በተሰኘ ፕሮጀክት ለተማሪዎች የተለያዩ የመማሪያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑን ጠቁመው ድጋፉ በኢትዮጵያ እና ቻይና መንግስታት መካከል ያለውን የቆየ ወዳጅነት የሚያጠናክር መሆኑንም አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው የቻይናው ፋውንዴሽን ፎር ሩራል ዴቭሎፕመንት በፓንዳ ፓክ ፕሮጀክት ለሚ ኩራ ለሚገኘውና ዘንድሮ ወደ መማር ማስተማር ስራ ለገባው ዱዱ ቢሳ 1 ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚማሩ ተማሪዎች ላደረገው የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ትምህርት ቤቱ አዲስ እንደመሆኑ ለተማሪዎች ምቹ የመማሪያ ስፍራ እንዲሆን የሁሉንም ባለድርሻ ድጋፍ እንደሚፈልግ በመግለጽ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮም ለትምህርት ቤቱ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል።

ፋውንዴሽኑ ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ትምህርታቸው እንዳይስተጉዋጎል በማሰብ ላበረከተው የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ክፍተኛ ምስጋና እንደሚገባው የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ታረቀኝ ገመቹ ገልጸዋል።

በርክክብ መርሀ ግብሩ ለዱዱ ቢሳ 1ኛ ደረጃ እና ባቅራቢያው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ 1,913 ተማሪዎች የሚያገለግሉ ቦርሳዎች፣ደብተሮች፣እር ሳሶች፣ እስክሪፕቶዎች፣የንጽህና መጠበቂያዎችን ጨምሮ የውሀ ኮዳዎችና የዝናብ ልብሶች ከእለቱ የክብር እንግዶች ለተማሪዎች ተበርክቱዋል።

 

 

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 0
  • 205
  • 6,046
  • 31,180
  • 147,475
  • 147,475