ለመምህራንና ለትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት የጽሁፍ ምዘና ተሰጠ፡፡

by | ዜና

(ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ.ም)  የጽሁፍ ምዘናው በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ 18 ሺ 591 መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች በ15 የመፈተኛ ጣቢያዎች የተሰጠ ሲሆን በምዘና ሂደቱ ከአንድ ሺ በላይ ፈታኞች ፣ ሱፐርቫይዘሮችና አስተባባሪዎች ተመድበው ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣታቸው ተገልጻል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኘው ገብሩ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ጋር የምዘና ሂደቱን በተመለከቱበት ወቅት እንዳስታወቁት የጽሁፍ ምዘናው የመምህራንን የሙያ ብቃት በማሳደግ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እንዲቻል ታስቦ ዘንድሮ ለአምስተኛ ጊዜ መሰጠቱን ገልጸው ምዘናው የመምህራኑን ፍቃደኝነት መሰረት አድርጎ እንደመሰጠቱ  ተማሪዎች የተሻለ ትምህርት ማግኘት እንዲችሉ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ምዘናው በአማርኛ ፣አፋን ኦሮሞ እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች በ36 የትምህርት አይነቶች የተሰጠ ሲሆን የጽሁፍ ምዘናው ከ80% እንደሚያዝና ቀሪው 20% ደግሞ የማህደረ ተግባር ምዘናን መሰረት አድርጎ እንደሚያዝ ቀደም ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መገለጹ ይታወቃል፡፡

0 Comments

SITE VISITORS

  • 1
  • 187
  • 249
  • 2,423
  • 8,975
  • 243,957
  • 243,957