በ 2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ህዳር 12/2016 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ማሳሰቢያ፡ –
ከታች የተዘረዘሩ ዩኒቨርሲቲዎች የ Remedial ፕሮግራም የማያስተናግዱ መሆኑን እንገልጻለን።
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
- አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
- አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
- አርሲ ዩኒቨርሲቲ
- ኮተቤ የትምህርት ዪኒቨርሲቲ
ትምህርት ሚኒስቴር
0 Comments